የተረት መጽሐፍ ፖስተር

Sponsor My Book: Promote Your Product & Services

 

አሁን ላይ በአገራችን በአይነቱ ብቸኛው እና ልዩ የሆነውን “ታታ” በሚል ርእስ የተሰጠው የሕፃናት መፅሐፍ አዘጋጅቼ ጨርሻለው፤‘ታታ’ ስያሜውን ያገኘው የብዙ ህፃናት አፍ መፍቻ ከሆኑት ቃላቶች መካከል ታታ፣ ባባ፣ ማማ፣ ናና፣ ወዘተ የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ። ምናልባትም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህፃናት እነዚህን ቃላቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመውት ይሆናል። ከዚ ባሻገር ‘ታታ’ን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ለየት ያለ ቃል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የእናት ጡት የሚል ትርጓሜ ስላለው ነው። እንግዲ ሁሉም ህፃን ልጅ መጀመርያ የሚመገበው ምግብ የእናት ጡት የሚሰጠውን ወተት ነው፤ ይህም ከሌሎች ምግቦች ሁሉ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ይበልጥ የህፃናትን ጤንነት እና አካላዊ እድገትን የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል። ይሄ መፅሀፍም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች በላይ የህፃናትን አእምሮ ለማሳደግ የፈጠራ ችሎታቸውን እና አስተዋይነታቸውን ለመጨመር የተዘጋጀ ሲሆን የህፃናቶች ተቀዳሚ የአዕምሮ ምግባቸው እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።

“ታታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አሳታፊ እና ሰዕላዊ መፅሐፌ በ ‘ኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር’ የመፅሐፉ ረቂቅ በደንብ ተገምግሞ እና አስተያየት ተሰጥቶበት ለህትመት በቂ እና ለመላው ህዝብ ለየት ባለ መልኩ ቆንጆ ስራን ይዤ እንደቀረብኩ ተነግሮኛል። መፅሐፉ በአጠቃላይ ሀገራችን ላይ መኖር ካለባችው ነገር ግን እስካሁን ያልተሰራባቸው ነገሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀ ነው፤ ይህም ልዩ ያደርገዋል በመሆኑም የማንበብ ፍላጎትና እና ባህላችንን ሊያስተዋውቅ የሚችል፣ የኛን አገር ሊወክል የሚችል የባህል፣ የእምነት፣ የስርአት እንዲሁም የአመለካከት እና የአስተሳሰብ እድገትን ሊያመጡ የሚችሉ ልዩ ልዩ ነገሮች በመፅሀፍቶቹ ይዘት ውስጥ ተካትተዋል።  ይህም መፅሀፍ በተለያዩ እትሞች ታትሞ ለመላው ህዝብ ሲዳረስ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ትልቅ እና መልካም የሚባል ተፅእኖ ይኖረዋል፤ የዚህ መፅሐፍ ስፖንሰሮችም ትልቁን ሚና ይጫወታሉ የሚል እምነት አለኝ።

መፅሀፉ ታትሞ እንዳለቀ ብዙ ህዝብ በተገኘበት፣ ከተለያዩ ተቋማት የሚመጡ እንግዶች እና ልዩ እንግዶች በተሰበሰቡበት፣ የአርት (ስነ – ጥበብ) አፍቃሪያን በሙሉ በታደሙበት ሁኔታ የምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል። በዝግጅቱም ላይ በሀገራችን ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ጣብያዎች መጥተው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡ ጥሪ ይደረግላቸዋል። በሀገራችን  ያሉ ከትንሽ እስከትላልቅ ደረጃ ላይ ላሉ ድርጅቶችና ተቋማት እንዲገኙ እና አርትን እንዲደግፉ ጥሪ ይደረግላቸዋል። ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በዚህ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ አጋር ቢሆኑ በጣም ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለው፤ ከዛም ባለፈ አርትን እና አርቲስቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ስለሚያሳዩበት በብዙሀኑ ዘንድ አሁን ካላቸው በላይ ጥሩ እይታን ያገኛሉ ብዬ እገምታለሁ።

ስፖንሰርሺፑን ብዙ አማራጮች እንዲኖሩት እና እንደምትፈልጉት አይነት ስፖንሰር ለማማረጥ ይረዳቹ ዘንድ የሚከተሉትን ደረጃዎች እና ማብራሪያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ ከተቀመጡት ምርጫዎች እና አማራጮች ውጪ ግን ከእናንተ ፖሊሲ እና ህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ማርኬቲንግ ህጎችጋር ሊሄድ የሚችል ሌላ አማራጭ አለን የምትሉት ካለ ብታሳውቁኝ ደስ ይለኛል። Drop your Email Address

memorial for Ethiopian legends

“ ማካበድ አይሁንብኝና…. እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ”

“ ማካበድ አይሁንብኝና…. እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ”
‘እኛ ኢትዮጵያውያን ልዩነታችን ልዩ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ነን’

‘ አድዋ ‘ የአፍሪቃ ድል፣ የኩራታችን ምንጭ … ምናምን እያልኩ አለም የሚያውቀውን ፀሃይ የሞቀውን አኩሪ የድል ታሪክ እና እውነታ እየሰበኩ ሰውን ማዛግ አልፈልግም ፤ ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ነው ምገባው…ቆይ ቆይ ግን ከዛ በፊት…ምን ነክቷት ነበር ጣሉካ? ምን አስባ ነው ያኔ??..ግጥሚያው እግር ኳስ መስሏት ነው እንዴ!!⚽️

ሚገርመው ነገር ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ‘ ቅኔ ‘ ማለት ነን! ላያችንን አይተው እንኳን ሊያውቁን ሊገምቱን እንከብዳቸዋለን! ከስር ሲሉን ከላይ፣ መሀል ሲሉን ከዳር፣ ደካማ ሲሉን ሀያል ብርቱ… ብቻ ኢትዮጵያ ለጠላት strategy የማትመች፣ በፍቅር እንጂ በብልጣብልጥነትና በአጉል አራድነት ማትሸወድ ማትሸነፍ ናት( አንቀጽ 17፣ውጫሌ ስምምነትን ማስታወስ ግድ ይሉአል)
እና ይቺ ሰላቶ በወቅቱ የነበረብንን ዘርፈ ብዙ ልዩነቶች እንደ opportunity በመቁጠር፣ በቴክኖሎጂ ኋላ ቀር መሆናችንን እንደ ድክመታችን በማየት strength እና treats የሚባሉትን መሰረታዊ ጥናቶች እምብዛም ሳታደርግ ለፍልሚያ ተሰናዳች። ታዲያ እኛ ከልዩነታችን አንድነታችን ከኋላ ቀርነታችን ወኔያችን ያይላልና ጣሉካ ያሰበችው ያለመችው ሳይሳካ ቀርቶ የኢትዮጵያ እግር ስር ተብረክርካ ወደቀች፣ ተሸነፈች።??????
እውነት ለመናገር ኢትዮጵያ ለመግዛት እንጂ ለመገዛት የማትመች፣ ለመምራት እንጂ ለመመራት ያልተፈጠረች፣ ይሄ ነው የማይባል ዓንዳች ሀይል አብሯት ያለ ቅኔ የሆነች ሀገር ነች። ይሄን የምለው ኒዩትራል ሆኜ እንደ አንድ ፈጥረት፣ ለማንም እንደማያደላ ፍጡር ሆኜ እንጂ ራሴን እንደ 1 ኢትዮጵያዊ አይቼ አደለም።
በአድዋ ጦርነት ላይ ሀገራቹን ቸል ያላላቹ፤ ይልቁንም ደማቹን ያፈሰሳቹ፣ አጥንታቹን የከሰከሳቹ፣ በፀሎቱም ያገዛቹ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፋቹ ሠማዕታን በሙሉ ከልብ አመሰግናለው። ፈጣሪ ነብሳቹን በበጎ ይቀበላት፤ አሜን!

ቃለአብ ማቲዎስ 2012/2020
ይህቺ የጥበብ ስራ እና ፅሁፍ በአድዋ ጦርነት ላይ ለተሳተፉ ሰማእታት በሙሉ እንደመታሰቢያ ትሁንልኝ!

memorial for Ethiopian legends
Adwa Ethiopian as well as african victory
madela poster

ኢትዮጵያን ማብቃት

  • የሚከተለው ጽሁፍ ሌሎች ሰዎችጋም እንዲደርስ በጎ ተጽዕኖም ይኖረው ዘንድ share እና tag እናድርግ።እነሆ ደራሲ ወይም ጸሃፊ አይደለሁምና ከቃላት አሰካክ እና አጣጣሌ ይልቅ ሃሳቡ ላይ ታመዝኑልኝ ዘንድ እማጸናለው። እና ይህቺን አጭር ጽሁፍ ከጸሃፊው እውቅናና ፈቃድ ውጪ በከፊልም ይሁን በሙሉ በማንኛውም ዘመነኛ መልኩ ማባዛትም ሆነ ማሰራጨት መብታቹ ነው!…. መልካም ንባብ!

የ ኢትዮ ፊልሞች ብዙም አይመቹኝም! ከሌላው አለም አወዳድሬው ሳይሆን እንዲው ብሽቅ ብግን የሚያረጉ ብዙ ነገሮች ስለማይ ነው፤ በዚህም ምክንያት ኢትዮጲያ ውስጥ የሚሰሩ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን (ፊልሞች)ን ማየት ካቆምኩ ረዥም ግዜ ሆኖኛል፤ ይሁን እንጂ በአንድ አጋጣሚ ይሄን ‘ወደ ኋላ’ የተሰኘ ግሩም ፊልም ለማየት ቻልኩ፤ ፊልሙ መቼ ሲኒማ ላይ እንደዋለ ምንም የማውቀው ታሪክ የለም በቃ አየውት ወደድኩት! እና ሌላ የማላውቀው ነገር ቢኖር ከዚ በኋላ ስንት ግዜ እየደጋገምኩ እንደማየው ነው ። ለእኔ አንድ ፊልም ጥሩ ፊልም ለመባል እያዝናና የሚያስተምር፣ የ ገጸ-ባህርያቶቹ ስሜት እንዲሁም የፊልሙ እሳቤ ወደ ተደራሲያኑ መተላለፍ ሲችል፣ ድምጽ እና መብራት አጠቃቀም፣ የ ገጸ-ባህርያት መረጣ እና ችሎታ እንዲሁም በዋናነት ፊልሙ በ ማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው የበጎ ተጽዕኖ መጠን የሚሉት ጥቂት መስፈርቶቼ ናቸው። ፊልሙ ፍጹም ኢትዮጵያዊነታችንን ፍንትው አርጎ ያሳየ፤ ጀግንነታችን በጦርሜዳ ላይ ብቻ እንዳልነበረ ይልቁንም በዕደ ጥበብ፣ በስነ ህክምና፣ በስነ ሰዕል፣ በስነ ፈለክ፣ በኪነ ህንጻ፣ በስነ ህግ፣ በስነ ጽሁፍ፣ በስነ ታሪክ፣ በስነ ምርምር(ስነ መንፈስ) በመሳሰሉት የአእምሮ ግኝቶች ላይም እንደነበር ያሳያል ለዚህም የ’ፊልሙ አዘጋጅ እና ደራሲ ማህሙድ ዳውድ’ እንዲሁም ‘ቀይ ቀበሮ ምስሎች’ ምስጋና ይገባቸዋል ባይ ነኝ።

ወደ ቁምነገሩ ስመለስ ኢትዮጵያ ሃገራችንን ወደ ቀድሞ ታሪኳ እና ወደ ሃያልነቷ ለመመለስ ማንንም ሳንፈልግ የማንም እርዳታ እና ገንዘብ ሳያስፈልገን እኔ እና እናንተ ብቻ በመሆን ለምን ታሪክ አንሰራም?…እ? ምናልባት እንዴት ወዴት ምናምን የሚሉ ጥያቄዎችን ልትጥይቁ ትችላላቹ። ለነዚ ሁሉ ከባድ መሳይ ጥያቄዎቻቹ ግን የምሰጣቹ ማለፊያ መልስ ቢኖር…”ራሳችንን በማክሰም” የሚለው ነው።አዎ ይሄ ማለት ከራሳችን በላይ ለተከታይ ትውልድ ለመጪው ግዜ ተረካቢ ማሰብ ማለት ነው። ወንድም እህቶቼ አንድ መስማት ማትፈልጉት ግን ደሞ እውነት የሆነ ነገር ልንገራቹ በእኛ የህይወት ዘመን የግል ኑሯችሁን ታሻሽሉ ይሆናል እንጂ ኢትዮጲያችን በጭራሽ ካደጉ ሀገራት ተርታ ልትሰለፍም ሆነ ልትመደብ አትችልም! ቁርጣችሁን እወቁት እንግዲ።ከኛ በታች ያሉትም የኛን ፈለግ ነውና ሚከተሉት ልክ እንደኛ ለራሳቸው ኖረው ለራሳቸው ይሞታሉ ግብአተ መሬታቸውም ይከናወናል ህይወትም ይቀጥላል ሀገራችንም መንፏቀቋን ትቀጥላለች።እኛ አራዳ ትውልዶችም አይደለን? ይሄ እንዲፈጠር ከቶ አንፈቅድም! እስኪ አስቡት ያኔ ስልጣኔያችን ጫፍ በደረሰበት ዘመን፣ ኢትዮጵያያያ… ሲባል መላው አለም በሚርበደበድበት ግዜ ይሮሩ የነበሩትን ዘመዶቻችንን! ምን ጭንቀት ምንስ ችግር ነበር? ሳስበው ግን እነዛ የጥንት ዘመዶቻችን ፤ አያት አባቶቻቸው እንዴት አድርገው ለዛ ክብር እንዳበቋቸው የተረዱ አይመስለኝም ቢሆንማ ኖሮ ከጀብዳችን ታሪክ እኩል ጥበብን፣ፈጠራን እንዲሁም ምርምር አደራረግ መንገዱን በቀሰሙ ነበር ቀስመውም ለልጅ ልጆቻችው ማስተላለፍ በቻሉ ነበር እኛም ይሄን ግዜ በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚው እንዲሁም በተለያዩ ዘርፎች ግንባር ቀደም ሆንን በመራን ነበር። አሁን እየሄድን ባለንበት አካሄድ ጥቂት ለውጥ ወይም ከሌላው አለም አንጻራዊ የፍጥነት እርምጃ ላይ ልንደርስ እንችል ይሆናል ለመድረስ በምናረገው ፍጭርጭሪት ግን የሆነ ቦታ ላይ መዳከም ከመጣ ከበፊቱ በላይ ርቀታችን ይሰፋል ስለዚ ራሳችንን በማክሰምና በቀጣዩ ትውልድ ላይ አቅምን አሰባስቦ ወይ በመሮጥ ወይ ረጅም መሳይ አቋራጭ መንገድ በመጠቀም ልንደርስባቸው ይገባል።

ራሳችንን እናክስም! አሁን ካለንበት ዘመናዊ ባርነት እኛ መውጣት ባንችልም ቀጣይ ትውልዶቻችን ግን ነጻ እንዲወጡ ማድረግ እንችላለን። ያደገ ሀገር ያደገ ኑሮ ብልጭልጩ ሁሉ ያጓጓን ይሆናል! እነሆ ሰው ነንና ልንጓጓም ይገባል። እላፊ መፈለጋችን ግን ባርያቸው ቢያደርገን እንጂ ክብራችንን አይመልስልንም ከዛ ይልቅ አብዝቶ ለሚፈልገን እላፊ ለሚጓጓልን ህዝብ፡ ሰው እንሁንለት …ንጉስም ያደርገናል ከዙፋኑ ማማም ያስቀምጠናል።አሁን ላይ አብዛኞቻችን የተማርን የተመራመርን የምንባል እኛ እውነት ምንድነው የተማርነው ምንስ ነው የተመራመርነው? እሺ ምርምራችን ለወረቀት ነበር ወይስ የእውነት የሃገራችንን ቁልፍ ችግር መፍታት የሚያስችል ሲያንገበግበን የነበረ ነገር ነው?… እኔ በመሰረቱ የንድፍ ባለሙያ (Designer)ነኝ እስካሁን ግን ኪሴን ሚያሳድግልኝ ነገር እንጂ የሃገሬን ክብር ሊያስጠብቅ ፣ የሃገሬን ሰው ሊያነቃቃ የሚችል፣ የሃገሬን ዘርፈ ብዙ ጥበባቶች እኔ በተሰማራውበት ዘርፍ በበቂ ሁኔታ ሊያሳድግ የሚችል ስራን ሰርቼያልው ብዬ ስለማላስብ ጸጸት ይሰማኛል። ደግሞም መምህር ነኝ ያውም ብዙ ትውልድ ለመቅረጽ የሚያስችል ቁልፍ ቦታ ላይ የምገኝ በአስተምሮቴ ካሪኩለሙ ሚያዘውን ሞጁሉ ሚለውን ብቻ ሳይሆን ተማሪ ትክክለኛ ማንነቱን ፈልጎ ሚያገኝበትን መንገድ እና እድሉን ሚፈጥርበትን ስርአት ለመቅረጽ የምጥር! ይሁን እንጂ ጥረቴ በቂ እንዳልሆነ ይሰማኛል እና በዚህም ተጨማሪ ጸጸት ይሰማኛል። ልብስ ሰፊ፣ ሃኪም ዶክተር፣ ሾፈር፣ አናጺ፣ አርቲስት( All artists and designers, decorative and fine artists, etc), ዳኛ ወዘተ… ሙያ ውስጥ ያለን ምን ያህል ኢትዮጲያ ላይ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ስራን ለመስራት አስበን እናውቃለን ሃሳቡስ ምን ያህል ማህበረሰብ ላይ በጎ ተጽዕኖ ነበረው? ይሄን ሃሳባችንንስ እንዳናሳካው ምንድን ነበር የያዘን? አዎ እነዚህ ሁሉ ሃሳቦች በጋራ ሲሆኑ በጣም ቀለል ይላሉ እንዲሁም ይበልጥ ሊዳብሩ እና ወደመሬትም በቀላሉ ሊወርዱ ይችላሉ። አንተ የጎደለህን ሃሳብ እሷ ትሞላዋለች፣ እሷ የተቸገረችበትን እቅድ አንተ ታረቅላታለህ፣ የኔን የመፍትሄ ሃሳብ ታሻሽልልኝኛለህ አንቺም ትገመግሚልኛለሽ፤ እኛው ከስመን፣እኛው ለኛዪቱ ምስኪኒቱ ድሃይቱ ሃገራችን መድሃኒት፣ ለእድገቷም ምክንያት መሆን እንችላለን። ቸር ያቆየን!
ቃለአብ ማቲዎስ kalex mat
ታህሳስ 26 2012.

DIRE DAWA

photo manipulation Dire Dawa, ethiopia

by Architect and graphics designer Kaleab Matiwos

DIRE DAWA

Dire Dawa is city in Harar region, Ethiopia. It is a commercial and industrial center located on the Addis Ababa–Djibouti railroad. Manufactures include processed meat, vegetable oil, textiles, and cement. There are also railroad workshops in the city. Dire Dawa was founded in 1902 when the railroad from Djibouti reached the area, and its growth has resulted largely from trade brought by the railroad.

in the above illustrated picture that express dire in one photo which is designed by Designer Kaleab Matiwos. As Dire Dawa has a rich wealth of pre-historic cave paintings some of which have achieved international recognition through the efforts of the French and American Geologists that have studied them several times in the last 75 years, while there are still other caves that have never been studied so far, those cave paints are inluded in the illustrated picture above in a futuristic way.

In the middle of the illustration Designer Kaleab included camels, peoples with different life style and culture also kefira market. Kefira is a traditional market place where one can see the colorful presentation of all people of the region in their cultural dresses. The presence of camels, donkeys, and the inevitable Gharris, two wheeled carts drown by a horse or a mule, gives it an aura of going back to medieval times.

source : – http://www.selamta.net/