kaleXmat

Welcome to Kalexmat.com - Your #1 Source for Creative Arts and Designs.

Sale!

Best children’s storey book Tata | የልጆች ተረት መጽሀፍ

Original price was: Br150.00.Current price is: Br99.00.

you can purchase this book with a great discount by contacting directly to the Author, call +251910969332  

This illustrated Children’s book, titled ‘TATA’, after the draft has been thoroughly reviewed and commented on by ‘Ethiopian Writers Association’ I’ve been told that I’ve come up with a beautiful work that is unique enough to be published, and to the general public. The book focuses on things that should exist in our country as a whole but has not yet been done; this makes it unique and can promote our interest in reading and culture; The content of the book includes a variety of factors that may represent our country that may contribute to the development of culture, beliefs, systems, and attitudes. When this book published in various editions and distributed to the general public, it will have a profound and positive impact on millions of people

Availability: 200 in stock

SKU: 3 Category:

 

አስተማሪና አዝናኝ ሰዕላዊ የህፃናት መፅሐፍ

“በውስጡም የህፃናትን የፈጠራና የመመራመር ክህሎታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉ የተለያዩ አሳታፊ (Interactive) ተግባሮችን የያዘ”

you can purchase this book with a great discount by contacting directly to the Author, call +251910969332  

My engaging and illustrated Children’s book, titled ‘TATA’, after the draft has been thoroughly reviewed and commented on by ‘Ethiopian Writers Association’ I’ve been told that I’ve come up with a beautiful work that is unique enough to be published, and to the general public. The book focuses on things that should exist in our country as a whole but has not yet been done; this makes it unique and can promote our interest in reading and culture; The content of the book includes a variety of factors that may represent our country that may contribute to the development of culture, beliefs, systems, and attitudes. When this book published in various editions and distributed to the general public, it will have a profound and positive impact on millions of people

‘ታታ’ ስያሜውን ያገኘው የብዙ ህፃናት አፍ መፍቻ ከሆኑት ቃላቶች መካከል ታታ፣ ባባ፣ ማማ፣ ናና፣ ወዘተ የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ። ምናልባትም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህፃናት እነዚህን ቃላቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመውት ይሆናል። ከዚ ባሻገር ‘ታታ’ን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ለየት ያለ ቃል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የእናት ጡት የሚል ትርጓሜ ስላለው ነው። እንግዲ ሁሉም ህፃን ልጅ የመጀመርያ የሚመገበው ምግብ የእናት ጡት የሚሰጠውን ወተት ነው፤ ይህም ከሌሎች ምግቦች ሁሉ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ይበልጥ የህፃናትን ጤንነት እና አካላዊ እድገትን የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል። ይሄ መፅሀፍም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች በላይ የህፃናትን አእምሮ ለማሳደግ የፈጠራ ችሎታቸውን እና አስተዋይነታቸውን ለመጨመር የተዘጋጀ ሲሆን የህፃናቶች ተቀዳሚ የአዕምሮ ምግባቸው እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል። አንድን የባህር ዛፍ ችግኝ በችግኝነቱ ግዜ ከተንከባከብነውና ቀጥ ብሎ እንዲያድግ የተለያዩ መንገዶችን ብንጠቀም ይሳካልናል፣ ከጥቂት ወራት ወይም አመት በኋላ የተስተካከለ እና ያማረ ለፈለግነው አላማ ልናውለው የምንችለው ጥሩ ግንድ ሆኖ እናገኘዋለን፣ ከመነሻው የተጣመመ እና እንክብካቤ ያልተሰጠው ያደገ የዛፍ ግንድን ግን ለማስተካከል በጣም ፈታኝ ነው።ይሄ ምሳሌም ህፃናትን ይወክላል፣ ህፃናትም የተስተካከለ ስብዕና፣ ለሀገር አሳቢና ተቆርቋሪ፣ ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ፣ ታላቆቻቸውን አክባሪ እና ስርአት ያላቸው ጥሩ ሰው እንዲሆኑ ገና ለጋ እድሚያቸው ላይ እንክብካቤና ትኩረት ይፈልጋሉ። ለዚህም ገና ከህፃንነታቸው ጀምሮ የማንበብን ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ ህፃናትን በመልካም ከሚቀርፁ መንገዶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ነው። ከዚህ አንፃር ይህ መፅሐፍ በውስጡ ብዙ ነገሮችን የሚዳሥሥ ሲሆን ከሌሎች መፅሐፍቶች በብዙ ነገሮች ልዩ ሆኖ መምጣት ችሉሏል ለምሳሌ ያክል የሴቶችን እና የወንዶችን በባህላችን ምክንያት የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ ተሞክሯል።

እንደሚታወቀው ሴቶች እና ወንዶች አሁን ላይ ያላቸው የተሳትፎ፣ ነገሮችን ለመሞከር ያላቸው ድፍረት እና ዘርፈ ብዙ ነገሮች ላይ ያላቸው አቋም በጣም የተለያየ ነው! ይህም ከህፃንነታችን ጀምሮ ጥቃቅንም ይሁኑ ከባድ አብረውን ያደጉ የተለያዩ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። ይሕም የራሱ የሆነ አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች አሉት ታዲያ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ይህንን መሰረት ያደረገ አነስተ

ኛም ቢሆን ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሁነት በውስጡ ይዟል ፣ ኢትዮጵያዊ ባህል፣ አለባበስ፣ አኗኗርን እና ጥሩ የሚባሉ የሀገራዊ እሴቶችን ይበልጥ ለማጠንከር ያስችላል በዚህም ስለሀገራቸው ሊኖራቸው የሚችለውን ፍቅር እና ትኩረት በእጅጉ ያሻሽላል፣ በመፅሐፉ ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህፃናቱ(የሚያነቡት) የጎደሉ እና በከፊል ቀለም የተቀቡ ምስሎችን በተለያዩ የእርሳስ ቀለማት እንዲሞሉ እና እንዲስሉባቸው የተዘጋጁ ገፆች አሉ ይሄም አንባቢዎቹ ህፃናት ማንበብ ብቻ ሳይሆን የጎደለውን በመሙላት የመፅሐፉ ተሳታፊ የሆኑ ያክል እንዲሰማችው ያደርጋል።

ከዚህጋም ተያይዞ አዕምሮዋቸው በፈቀደና ስሚታቸውን ባስደሰታቸው ልክ ስለሚሞነጫጭሩበት፣ ለጋ አዕምሮአቸው ለፈጠራና አዲስ ነገሮችን ለመስራት ሙሉ የአዕምሮ ነፃነትን ያገኛል ይሄም በሌላ ነገሮች ከሚያገኙት በራስ መተማመን እና መንፈሳዊ ጥንካሬ በላይ ጥሩ እድልን ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይታሰባል፣ ታላላቆችን ማክበር እና የሚመከሩትን ነገር መቀበል ስለሚሰጠው ጠቀሜታ እንዲሁም ምን ያህል እንደሚረዳቸው ግንዛቤ ያስጨብጣል። ይሄንን የመሳሰሉ እና ሌሎች ያልተጠቀሱ ነገሮች ይህን መፅሐፍ ልዩ እና የመጀመርያው ያደርገዋል።

 

Weight 10 kg
Dimensions 50 × 60 × 40 cm
Scroll to Top