kaleXmat

Welcome to Kalexmat.com - Your #1 Source for Creative Arts and Designs.

Tag: children book covers

Best children’s book Tata

አስተማሪና አዝናኝ ሰዕላዊ የህፃናት መፅሐፍ

“በውስጡም የህፃናትን የፈጠራና የመመራመር ክህሎታቸውን ሊያዳብሩ የሚችሉ የተለያዩ አሳታፊ (Interactive) ተግባሮችን የያዘ”

you can purchase this book with a great discount by contacting directly to the Author, call +251910969332  or +251919369844

My engaging and illustrated Children’s book, titled ‘TATA’, after the draft has been thoroughly reviewed and commented on by ‘Ethiopian Writers Association’ I’ve been told that I’ve come up with a beautiful work that is unique enough to be published, and to the general public. The book focuses on things that should exist in our country as a whole but has not yet been done; this makes it unique and can promote our interest in reading and culture; The content of the book includes a variety of factors that may represent our country that may contribute to the development of culture, beliefs, systems, and attitudes. When this book published in various editions and distributed to the general public, it will have a profound and positive impact on millions of people

 

Design by Kalexmat

‘ታታ’ ስያሜውን ያገኘው የብዙ ህፃናት አፍ መፍቻ ከሆኑት ቃላቶች መካከል ታታ፣ ባባ፣ ማማ፣ ናና፣ ወዘተ የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ። ምናልባትም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህፃናት እነዚህን ቃላቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመውት ይሆናል። ከዚ ባሻገር ‘ታታ’ን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ለየት ያለ ቃል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የእናት ጡት የሚል ትርጓሜ ስላለው ነው። እንግዲ ሁሉም ህፃን ልጅ የመጀመርያ የሚመገበው ምግብ የእናት ጡት የሚሰጠውን ወተት ነው፤ ይህም ከሌሎች ምግቦች ሁሉ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ይበልጥ የህፃናትን ጤንነት እና አካላዊ እድገትን የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል። ይሄ መፅሀፍም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች በላይ የህፃናትን አእምሮ ለማሳደግ የፈጠራ ችሎታቸውን እና አስተዋይነታቸውን ለመጨመር የተዘጋጀ ሲሆን የህፃናቶች ተቀዳሚ የአዕምሮ ምግባቸው እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል። አንድን የባህር ዛፍ ችግኝ በችግኝነቱ ግዜ ከተንከባከብነውና ቀጥ ብሎ እንዲያድግ የተለያዩ መንገዶችን ብንጠቀም ይሳካልናል፣ ከጥቂት ወራት ወይም አመት በኋላ የተስተካከለ እና ያማረ ለፈለግነው አላማ ልናውለው የምንችለው ጥሩ ግንድ ሆኖ እናገኘዋለን፣ ከመነሻው የተጣመመ እና እንክብካቤ ያልተሰጠው ያደገ የዛፍ ግንድን ግን ለማስተካከል በጣም ፈታኝ ነው።

Design by Kalexmat

ይሄ ምሳሌም ህፃናትን ይወክላል፣ ህፃናትም የተስተካከለ ስብዕና፣ ለሀገር አሳቢና ተቆርቋሪ፣ ፈጣሪያቸውን የሚፈሩ፣ ታላቆቻቸውን አክባሪ እና ስርአት ያላቸው ጥሩ ሰው እንዲሆኑ ገና ለጋ እድሚያቸው ላይ እንክብካቤና ትኩረት ይፈልጋሉ። ለዚህም ገና ከህፃንነታቸው ጀምሮ የማንበብን ልምድ እንዲያዳብሩ ማድረግ ህፃናትን በመልካም ከሚቀርፁ መንገዶች መካከል አንዱ እና ዋነኛው ነው። ከዚህ አንፃር ይህ መፅሐፍ በውስጡ ብዙ ነገሮችን የሚዳሥሥ ሲሆን ከሌሎች መፅሐፍቶች በብዙ ነገሮች ልዩ ሆኖ መምጣት ችሉሏል ለምሳሌ ያክል የሴቶችን እና የወንዶችን በባህላችን ምክንያት የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብ ተሞክሯል።

እንደሚታወቀው ሴቶች እና ወንዶች አሁን ላይ ያላቸው የተሳትፎ፣ ነገሮችን ለመሞከር ያላቸው ድፍረት እና ዘርፈ ብዙ ነገሮች ላይ ያላቸው አቋም በጣም የተለያየ ነው! ይህም ከህፃንነታችን ጀምሮ ጥቃቅንም ይሁኑ ከባድ አብረውን ያደጉ የተለያዩ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። ይሕም የራሱ የሆነ አሉታዊና አዎንታዊ ጎኖች አሉት ታዲያ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ ይህንን መሰረት ያደረገ አነስተኛም ቢሆን ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ሁነት በውስጡ ይዟል ፣ ኢትዮጵያዊ ባህል፣ አለባበስ፣ አኗኗርን እና ጥሩ የሚባሉ የሀገራዊ እሴቶችን ይበልጥ ለማጠንከር ያስችላል በዚህም ስለሀገራቸው ሊኖራቸው የሚችለውን ፍቅር እና ትኩረት በእጅጉ ያሻሽላል፣ በመፅሐፉ ውስጥ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህፃናቱ(የሚያነቡት) የጎደሉ እና በከፊል ቀለም የተቀቡ ምስሎችን በተለያዩ የእርሳስ ቀለማት እንዲሞሉ እና እንዲስሉባቸው የተዘጋጁ ገፆች አሉ ይሄም አንባቢዎቹ ህፃናት ማንበብ ብቻ ሳይሆን የጎደለውን በመሙላት የመፅሐፉ ተሳታፊ የሆኑ ያክል እንዲሰማችው ያደርጋል።

best children book
Design by kalexmat

ከዚህጋም ተያይዞ አዕምሮዋቸው በፈቀደና ስሚታቸውን ባስደሰታቸው ልክ ስለሚሞነጫጭሩበት፣ ለጋ አዕምሮአቸው ለፈጠራና አዲስ ነገሮችን ለመስራት ሙሉ የአዕምሮ ነፃነትን ያገኛል ይሄም በሌላ ነገሮች ከሚያገኙት በራስ መተማመን እና መንፈሳዊ ጥንካሬ በላይ ጥሩ እድልን ይፈጥርላቸዋል ተብሎ ይታሰባል፣ ታላላቆችን ማክበር እና የሚመከሩትን ነገር መቀበል ስለሚሰጠው ጠቀሜታ እንዲሁም ምን ያህል እንደሚረዳቸው ግንዛቤ ያስጨብጣል። ይሄንን የመሳሰሉ እና ሌሎች ያልተጠቀሱ ነገሮች ይህን መፅሐፍ ልዩ እና የመጀመርያው ያደርገዋል።

Design by Kalexmat

 

Sponsor My Book: Promote Your Product & Services

No Comments
የተረት መጽሐፍ ፖስተር

 

አሁን ላይ በአገራችን በአይነቱ ብቸኛው እና ልዩ የሆነውን “ታታ” በሚል ርእስ የተሰጠው የሕፃናት መፅሐፍ አዘጋጅቼ ጨርሻለው፤‘ታታ’ ስያሜውን ያገኘው የብዙ ህፃናት አፍ መፍቻ ከሆኑት ቃላቶች መካከል ታታ፣ ባባ፣ ማማ፣ ናና፣ ወዘተ የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ። ምናልባትም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህፃናት እነዚህን ቃላቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመውት ይሆናል። ከዚ ባሻገር ‘ታታ’ን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ለየት ያለ ቃል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የእናት ጡት የሚል ትርጓሜ ስላለው ነው። እንግዲ ሁሉም ህፃን ልጅ መጀመርያ የሚመገበው ምግብ የእናት ጡት የሚሰጠውን ወተት ነው፤ ይህም ከሌሎች ምግቦች ሁሉ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ይበልጥ የህፃናትን ጤንነት እና አካላዊ እድገትን የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል። ይሄ መፅሀፍም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች በላይ የህፃናትን አእምሮ ለማሳደግ የፈጠራ ችሎታቸውን እና አስተዋይነታቸውን ለመጨመር የተዘጋጀ ሲሆን የህፃናቶች ተቀዳሚ የአዕምሮ ምግባቸው እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።

“ታታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አሳታፊ እና ሰዕላዊ መፅሐፌ በ ‘ኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር’ የመፅሐፉ ረቂቅ በደንብ ተገምግሞ እና አስተያየት ተሰጥቶበት ለህትመት በቂ እና ለመላው ህዝብ ለየት ባለ መልኩ ቆንጆ ስራን ይዤ እንደቀረብኩ ተነግሮኛል። መፅሐፉ በአጠቃላይ ሀገራችን ላይ መኖር ካለባችው ነገር ግን እስካሁን ያልተሰራባቸው ነገሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀ ነው፤ ይህም ልዩ ያደርገዋል በመሆኑም የማንበብ ፍላጎትና እና ባህላችንን ሊያስተዋውቅ የሚችል፣ የኛን አገር ሊወክል የሚችል የባህል፣ የእምነት፣ የስርአት እንዲሁም የአመለካከት እና የአስተሳሰብ እድገትን ሊያመጡ የሚችሉ ልዩ ልዩ ነገሮች በመፅሀፍቶቹ ይዘት ውስጥ ተካትተዋል።  ይህም መፅሀፍ በተለያዩ እትሞች ታትሞ ለመላው ህዝብ ሲዳረስ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ትልቅ እና መልካም የሚባል ተፅእኖ ይኖረዋል፤ የዚህ መፅሐፍ ስፖንሰሮችም ትልቁን ሚና ይጫወታሉ የሚል እምነት አለኝ።

መፅሀፉ ታትሞ እንዳለቀ ብዙ ህዝብ በተገኘበት፣ ከተለያዩ ተቋማት የሚመጡ እንግዶች እና ልዩ እንግዶች በተሰበሰቡበት፣ የአርት (ስነ – ጥበብ) አፍቃሪያን በሙሉ በታደሙበት ሁኔታ የምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል። በዝግጅቱም ላይ በሀገራችን ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ጣብያዎች መጥተው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡ ጥሪ ይደረግላቸዋል። በሀገራችን  ያሉ ከትንሽ እስከትላልቅ ደረጃ ላይ ላሉ ድርጅቶችና ተቋማት እንዲገኙ እና አርትን እንዲደግፉ ጥሪ ይደረግላቸዋል። ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በዚህ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ አጋር ቢሆኑ በጣም ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለው፤ ከዛም ባለፈ አርትን እና አርቲስቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ስለሚያሳዩበት በብዙሀኑ ዘንድ አሁን ካላቸው በላይ ጥሩ እይታን ያገኛሉ ብዬ እገምታለሁ።

ስፖንሰርሺፑን ብዙ አማራጮች እንዲኖሩት እና እንደምትፈልጉት አይነት ስፖንሰር ለማማረጥ ይረዳቹ ዘንድ የሚከተሉትን ደረጃዎች እና ማብራሪያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ ከተቀመጡት ምርጫዎች እና አማራጮች ውጪ ግን ከእናንተ ፖሊሲ እና ህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ማርኬቲንግ ህጎችጋር ሊሄድ የሚችል ሌላ አማራጭ አለን የምትሉት ካለ ብታሳውቁኝ ደስ ይለኛል። Drop your Email Address