“ ማካበድ አይሁንብኝና…. እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ”
‘እኛ ኢትዮጵያውያን ልዩነታችን ልዩ ከመሆኑ የተነሳ አንድ ነን’
‘ አድዋ ‘ የአፍሪቃ ድል፣ የኩራታችን ምንጭ … ምናምን እያልኩ አለም የሚያውቀውን ፀሃይ የሞቀውን አኩሪ የድል ታሪክ እና እውነታ እየሰበኩ ሰውን ማዛግ አልፈልግም ፤ ቀጥታ ወደ ጉዳዬ ነው ምገባው…ቆይ ቆይ ግን ከዛ በፊት…ምን ነክቷት ነበር ጣሉካ? ምን አስባ ነው ያኔ??..ግጥሚያው እግር ኳስ መስሏት ነው እንዴ!!⚽️
ሚገርመው ነገር ኢትዮጵያና ህዝቦቿ ‘ ቅኔ ‘ ማለት ነን! ላያችንን አይተው እንኳን ሊያውቁን ሊገምቱን እንከብዳቸዋለን! ከስር ሲሉን ከላይ፣ መሀል ሲሉን ከዳር፣ ደካማ ሲሉን ሀያል ብርቱ… ብቻ ኢትዮጵያ ለጠላት strategy የማትመች፣ በፍቅር እንጂ በብልጣብልጥነትና በአጉል አራድነት ማትሸወድ ማትሸነፍ ናት( አንቀጽ 17፣ውጫሌ ስምምነትን ማስታወስ ግድ ይሉአል)
እና ይቺ ሰላቶ በወቅቱ የነበረብንን ዘርፈ ብዙ ልዩነቶች እንደ opportunity በመቁጠር፣ በቴክኖሎጂ ኋላ ቀር መሆናችንን እንደ ድክመታችን በማየት strength እና treats የሚባሉትን መሰረታዊ ጥናቶች እምብዛም ሳታደርግ ለፍልሚያ ተሰናዳች። ታዲያ እኛ ከልዩነታችን አንድነታችን ከኋላ ቀርነታችን ወኔያችን ያይላልና ጣሉካ ያሰበችው ያለመችው ሳይሳካ ቀርቶ የኢትዮጵያ እግር ስር ተብረክርካ ወደቀች፣ ተሸነፈች።??????
እውነት ለመናገር ኢትዮጵያ ለመግዛት እንጂ ለመገዛት የማትመች፣ ለመምራት እንጂ ለመመራት ያልተፈጠረች፣ ይሄ ነው የማይባል ዓንዳች ሀይል አብሯት ያለ ቅኔ የሆነች ሀገር ነች። ይሄን የምለው ኒዩትራል ሆኜ እንደ አንድ ፈጥረት፣ ለማንም እንደማያደላ ፍጡር ሆኜ እንጂ ራሴን እንደ 1 ኢትዮጵያዊ አይቼ አደለም።
በአድዋ ጦርነት ላይ ሀገራቹን ቸል ያላላቹ፤ ይልቁንም ደማቹን ያፈሰሳቹ፣ አጥንታቹን የከሰከሳቹ፣ በፀሎቱም ያገዛቹ፣ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፋቹ ሠማዕታን በሙሉ ከልብ አመሰግናለው። ፈጣሪ ነብሳቹን በበጎ ይቀበላት፤ አሜን!
ቃለአብ ማቲዎስ 2012/2020
ይህቺ የጥበብ ስራ እና ፅሁፍ በአድዋ ጦርነት ላይ ለተሳተፉ ሰማእታት በሙሉ እንደመታሰቢያ ትሁንልኝ!
