kaleXmat

Welcome to Kalexmat.com - Your #1 Source for Creative Arts and Designs.

ራስህን አትጥላ

እኔ በህይወቴ ስህተት ሰርቼ አዉቃለሁ ወደ ፊትም
ስህተት እንደምሰራ እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን አሁንም
ራሴን እወደዋለሁ። እዉነታዉ እኔ ሁል ጊዜ ትክክል
ላላደርግ እችላለሁ ይህ ማለት ግን ማን መሆኔን
አይነካዉም። እንደተወደድኩና አሁንም መልካም ሰዉ
እንደሆንኩ አዉቃለሁ።

ከሀፍረት ነጻ የሆነ አዲስ ነጻነት መለማመድ ትችላለህ።
እግዚአብሔር እንደወደደህ ስታስተዉል ራስህን
ጤናማና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መዉደድ
ትጀምራለህ። ራስህን መዉደድ ስትጀምር ሌሎች
ሰዎችም አንተን መዉደድ ይጀምራሉ። ራስን መዉደድ
ማለት በትዕቢት መሞላት ማለት አይደለም በቀላሉ
እግዚአብሔር አንተ እንድትሆን የፈጠረህን ማንነት
መቀበል ማለት ነዉ።

ሁላችንም በባህርያችን ለዉጥ እንፈልጋለን ነገር ግን
እግዚአብሔር እንደፈጠረን ራሳችንን መቀበል
በስሜታችን ጤናማ እንድንሆንና ለዉጥ እንድናመጣ
ወሳኝ ነገር ነዉ። ራሳችንን መዉደድን ብንችልበት
ሀፍረትን መሰረት ያደረገን ተፈጥሮ እንድናሸንፍ
ያግዘናል።

Discover more from kaleXmat

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Scroll to Top