kaleXmat

Welcome to Kalexmat.com - Your #1 Source for Creative Arts and Designs.

የኢትዮጵያ አዲሱ የብር ኖት እና በእኔ ላይ ያሳደረብኝ ጫና….

የኢትዮጲያ መንግስት አዲስ የብር ኖቶችን ለህትመት ለማብቃትና ለገበያ ለማዋል ዝግጅቷን ጨርሳ እንዳጠናቀቀችና ለ 2013 ወደ ብሄራዊ ባንክ ገቢ እንደሚደረግ ተገልጿል ታዲያ እኔ ምንድነው የተጎዳውት?…ምንስ ነው ያጣውት?…ነገሩ ምንድነው ከዚ ቀደም የአስር ብሩን ገንዘብ በመጠቀም ኢሉስትሬሽን ወይም ግራፊክስ ዲዛይን ሰርቼ ነበር። እርግጥ አንድ ሁለት አመት ሊያልፈው ይችላል እና በ አስር ብሩ ውስጥ የምትታየው ልጅ በወቅቱ ደስ ብሏት ነበር። አሁን ግን ከሷ በላይ ያዘነብኝ እና የተናደደብኝ ሰው ያለ አይመስለኝም… ጥያቄዋ እንደገባኝ ከሆነ 1,የኢትዮጲያ ብር ሊቀየር እንደሆነ እንዴት አታውቅም? እና ከቻልክ መልሰህ ስራልኝ! …ቆይ ግን እዚጋ….እኔ እንዴት ይሄን ልገምት እችል ነበር ? የአሁኑ አስር ብር ወደፊት ይቀየራል የሚል ምንም ግምቱ አልነበረኝም በርግጥ እንደ አንድ ዲዛይነር እነዚህን ነገሮች ማሰብ እና መገመት ነበረብኝ ቢሆንም ይሄ የአንድ ድርጅት ሎጎ ወይንም ደግሞ መለያ ምልክት አይደለም፣ እንደውም የድሮው ብር ላይ አርት ተሰርቶበት ለማስታወሻነት ቢቀመጥ ጥሩ ይመስለኛል እንግዲ በዚህ የብር ኖት መቀየር አነስተኛም ቢሆን የመጀመሪያው ጥቃት የደረሰበት ምስኪን  የኢትዮጵያ ዜጋ ለመሆን በቅቻለው…ሃሃሃ

 

Discover more from kaleXmat

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Scroll to Top