በቀጥታ የዩቲዩብ ቻናላችንን ለመጎብኘት 👉 ይሄን ይጫኑ Click Here
ላሊበላ በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከአንድ ወጥ ድንጋይ/አለት ተቆርቁረው ከተሰሩ ህንጣዎች መካከል በአይነቱም በይዘቱም ድንቅ የኪነህንጣ ጥበብ የሚስተዋልበት ውቅር ነው። መላው የላሊበላ ስልጣኔ ለጥንታዊቷ ፣ ለመካከለኛው ዘመን እና ከዛም በኋላ ለአሁኗ ኢትዮጵያ ስልጣኔ ደረጃ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ላሊበላ በመላው ክርስቲያን ዘንድ ከአክሱም ቀጥሎ ቅዱስ ከተማ በመባል ሲታወቅ የሃይማኖታዊ ጉዞዎች እና የቱሪስቶች መዳረሻም ነው። ከአክሱም በተለየም የላሊበላ ህዝብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ናቸው ፡፡ ኢትዮጵያ በ 4 ኛው ክፍለዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ክርስትናን ከተቀበሉ ቀደምት ሀገሮች አንዷ ስትሆን ታሪካዊ መሰረቷም ከሐዋርያት ዘመን ጀምሮ ነው ፡፡አብያተ ክርስቲያኖቹ ራሳቸው ከ 7 ኛው እስከ 13 ኛው ክፍለዘመን የተገነቡ ናቸው። በተለምዶ የዛጉዌ ንጉስ ገብረመስቀል ላሊበላም ዘመነ መንግስታቸው እንደነበር በብዙሃን ዘንድ ይነገራል ፡፡ በላሊበላ ውስጥ ያሉት ዋና ዋና ሕንፃዎች አቀማመጥ እና ስሞች የኢየሩሳሌም ተምሳሌት እና ውክልና ለማድረግ ታስበው የተሰሩ ሲሆን ይሄም በአካባቢው በሚኖሩ ሰዎች ይታመንበታል ይልቁንም በአካባቢው ባሉ ቀሳውስት በሰፊው ተቀባይነት አግኝቷል ፡፡….. የዩቲዩብ ቻናላችንን ለመጎብኘት 👉 ይሄን ይጫኑ Click Here