አሁን ላይ በአገራችን በአይነቱ ብቸኛው እና ልዩ የሆነውን “ታታ” በሚል ርእስ የተሰጠው የሕፃናት መፅሐፍ አዘጋጅቼ ጨርሻለው፤‘ታታ’ ስያሜውን ያገኘው የብዙ ህፃናት አፍ መፍቻ ከሆኑት ቃላቶች መካከል ታታ፣ ባባ፣ ማማ፣ ናና፣ ወዘተ የሚሉት ቃላቶች ይገኛሉ። ምናልባትም አብዛኞቹ የኢትዮጵያ ህፃናት እነዚህን ቃላቶች በተደጋጋሚ ተጠቅመውት ይሆናል። ከዚ ባሻገር ‘ታታ’ን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ለየት ያለ ቃል በመሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ የእናት ጡት የሚል ትርጓሜ ስላለው ነው። እንግዲ ሁሉም ህፃን ልጅ መጀመርያ የሚመገበው ምግብ የእናት ጡት የሚሰጠውን ወተት ነው፤ ይህም ከሌሎች ምግቦች ሁሉ ለሰውነት ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ስለያዘ ይበልጥ የህፃናትን ጤንነት እና አካላዊ እድገትን የተስተካከለ እንዲሆን ያደርጋል። ይሄ መፅሀፍም ደግሞ ከሌሎች ነገሮች በላይ የህፃናትን አእምሮ ለማሳደግ የፈጠራ ችሎታቸውን እና አስተዋይነታቸውን ለመጨመር የተዘጋጀ ሲሆን የህፃናቶች ተቀዳሚ የአዕምሮ ምግባቸው እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።
“ታታ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው አሳታፊ እና ሰዕላዊ መፅሐፌ በ ‘ኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር’ የመፅሐፉ ረቂቅ በደንብ ተገምግሞ እና አስተያየት ተሰጥቶበት ለህትመት በቂ እና ለመላው ህዝብ ለየት ባለ መልኩ ቆንጆ ስራን ይዤ እንደቀረብኩ ተነግሮኛል። መፅሐፉ በአጠቃላይ ሀገራችን ላይ መኖር ካለባችው ነገር ግን እስካሁን ያልተሰራባቸው ነገሮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀ ነው፤ ይህም ልዩ ያደርገዋል በመሆኑም የማንበብ ፍላጎትና እና ባህላችንን ሊያስተዋውቅ የሚችል፣ የኛን አገር ሊወክል የሚችል የባህል፣ የእምነት፣ የስርአት እንዲሁም የአመለካከት እና የአስተሳሰብ እድገትን ሊያመጡ የሚችሉ ልዩ ልዩ ነገሮች በመፅሀፍቶቹ ይዘት ውስጥ ተካትተዋል። ይህም መፅሀፍ በተለያዩ እትሞች ታትሞ ለመላው ህዝብ ሲዳረስ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ትልቅ እና መልካም የሚባል ተፅእኖ ይኖረዋል፤ የዚህ መፅሐፍ ስፖንሰሮችም ትልቁን ሚና ይጫወታሉ የሚል እምነት አለኝ።
መፅሀፉ ታትሞ እንዳለቀ ብዙ ህዝብ በተገኘበት፣ ከተለያዩ ተቋማት የሚመጡ እንግዶች እና ልዩ እንግዶች በተሰበሰቡበት፣ የአርት (ስነ – ጥበብ) አፍቃሪያን በሙሉ በታደሙበት ሁኔታ የምረቃ ስነ-ስርዓት ይከናወናል። በዝግጅቱም ላይ በሀገራችን ውስጥ ለሚገኙ የተለያዩ የቴሌቭዥን እና የሬድዮ ጣብያዎች መጥተው የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጡ ጥሪ ይደረግላቸዋል። በሀገራችን ያሉ ከትንሽ እስከትላልቅ ደረጃ ላይ ላሉ ድርጅቶችና ተቋማት እንዲገኙ እና አርትን እንዲደግፉ ጥሪ ይደረግላቸዋል። ስፖንሰር አድራጊ ድርጅቶች በዚህ ዝግጅት ላይ በመሳተፍ አጋር ቢሆኑ በጣም ጠቃሚ ነው ብዬ አስባለው፤ ከዛም ባለፈ አርትን እና አርቲስቶችን ለመደገፍ እና ለማበረታታት ያላቸውን ቁርጠኝነት ስለሚያሳዩበት በብዙሀኑ ዘንድ አሁን ካላቸው በላይ ጥሩ እይታን ያገኛሉ ብዬ እገምታለሁ።
ስፖንሰርሺፑን ብዙ አማራጮች እንዲኖሩት እና እንደምትፈልጉት አይነት ስፖንሰር ለማማረጥ ይረዳቹ ዘንድ የሚከተሉትን ደረጃዎች እና ማብራሪያዎች አዘጋጅቻለሁ፤ ከተቀመጡት ምርጫዎች እና አማራጮች ውጪ ግን ከእናንተ ፖሊሲ እና ህዝብ ግንኙነት እንዲሁም ማርኬቲንግ ህጎችጋር ሊሄድ የሚችል ሌላ አማራጭ አለን የምትሉት ካለ ብታሳውቁኝ ደስ ይለኛል። Drop your Email Address